የዘምዘም ባንክ አ.ማ. በምዝገባ ቁጥሩ MT/AA/3/0052093/2012 የተቋቋመ እና ዋና መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ የሆነው ባንክ፤ የባለአክሲዮኖች አንደኛ ጠቅላላ መደበኛ እና አስቸኳይ ድንገተኛ ጉባኤ ታህሳስ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ ሚድሮክ ግሩፕ ስር በሚገኘው መቻሬ ሜዳ አዳራሽ ስለሚያካሄድ፣ የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙልን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

 የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባዔውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየም፣
 2. ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
 3. የጉባዔውን ጸሐፊ መምረጥ፣
 4. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ፣
 5. እስከ 2012/13 ድረስ የተካሄዱ የአክሲዮን ዝውውሮችን መቀበል፣
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት መስማትና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 7. የባንኩን ቅድመ ምሥረታ በተመለከተ የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት መስማትና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 8. የባንኩን ዓመታዊ የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት መስማትና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 9. የአክሲዮን ግዢ የፈጸሙ የዲያስፖራ ባለአክስዮኖችን መስራችነት ማቅረብና ማጸደቅ፣
 10. ባለፈው ጉባዔ የተመረጠውን እያንዳንዱን የቦርድ አባል በድጋሚ በድምጽ ማስመረጥ፣
 11. በጎደሉ የቦርድ አባላት ቦታ ምትክ አባላትን መሾም፣
 12. የቦርድ አባላትን ወርሃዊና አመታዊ ክፍያ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት መወሰን፣
 13. የባንኩን የውጭ ኦዲተሮች መምረጥ እና ክፍያቸውን መወሰን፣
 14. በመስራችነት ቀርበው በተለያዩ ምክንያት ያልፈረሙ አባላትን በሚመለከት ማጸደቅ፣
 15. ፈርመው ክፍያውን ያልፈጸሙ አክስዮኖችን ማሰረዝ፣ እናየተጨማሪ አክስዮኖችን ሽያጭ ማጸደቅ፡፡

 

አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
 2. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ፣
 3. የባንኩን ዋና ገንዘብ ማሳደግ፣እና
 4. የባንኩን መተዳደሪያና መመሥረቻ ጽሑፍ ላይ በተደረገው የካፒታል ጭማሪ መሠረት ተገቢውን ማሻሻያ ማድረግ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

 • ባለአክሲዮኖች በጉባዔው ላይ ለመገኘት ኢትዮጵያዊነታቸውን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
 • በውክልና የሚገኙም ከሆነ የወካዩን ባለአክሲዮን ኢትዮጵያዊነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነት የሚያረጋግጥ መታወቂያ እና ቢጫ ካርድ ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ውክልና መስጠት የሚፈልግ ባለአክሲዮን ከህዳር 23 ቀን 2014  እስከ ህዳር 28 ቀን 2014  ድረስ በሥራ ሰዓት ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ይዞ በባንኩ ዋና መ/ቤት ጋራድ ሲቲ ሴንተር 12ኛ ፎቅ ፋይናንስና አካውንትስ መምሪያ በግንባር በመቅረብ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት መወከል ይችላል፡፡
 • በሠነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ወይም አግባብ ባለው አካል በተሰጠ ውክልና በስብሰባ የሚገኝ ተወካይ የወካዩን ኢትዮጵያዊነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነት የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር እና የውክልናውን ዋና ከኮፒ ጋር ይዞ መገኘት ይኖርበታል፡፡
 • በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣው መመሪያ የስብሰባ አዳራሾች በሚይዙት የተሰብሳቢ ብዛት ላይ ገደብ የተጣለ ስለሆነ ባለአክሲዮኖች በተቻለ መጠን ወኪል እንዲሾሙ፣ በጉባዔው ተሰብሳቢዎችም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡