የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ በአስመራጭኮሚቴ አማካይነት እንዲከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክባወጣው መመሪያ መሠረት የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድአስመራጭ ኮሚቴ በባንኩ የባለአክሲዮኖች 1 መደበኛጠቅላላ ጉባዔ መመረጡ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ኮሚቴው የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላትንጥቆማ 14 ቀን 2014 ዓ.ም /August 20, 2022/ እስከህዳር 11 ቀን 2015 . /November 20, 2022/ ብቻየሚቀበል ስለሆነ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥርSBB/71/2019 እና SBB/79/2021 ላይ የተዘረዘሩየሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩ የቦርድ አባላትንእንድትጠቁሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

1. የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ/ች፤
2. ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
3. በማንኛውም ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ/ች፤
4. ሀቀኛታማኝ እና መልካም ስብዕና ያለው/ያላት በተለይምበማጭበርበር እምነት በማጉደል ትክክለኛ ያልሆነየሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከስሶ/ተከስሳበፍ/ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሠጥቶበት የማያውቅ/የማታውቅ
5. በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ አባል ወይም ዋና ሥራአስፈፃሚ ያልሆነ/ነች
6. በንግድ ሥራና በንግድ ሥራ አስተዳደር በፋይናንስ ወይምበባንክ ሥራ የስራ ልምድ ያለው/ላት በተጨማሪምየሸሪዓ ግንዛቤ ያለው/ላት (ቢሆን ይመረጣል)
7. በራሱ/በራሷ ወይም በሚመራው/በምትመራው ወይምዳይሬክተር በሆነበት/በሆነችበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስያልቀረበበት/ያልቀረበባት ወይም የኪሳራ ውሳኔያልተሰጠበት/ባት
8. በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያ ያልተወሰደበት/ባት
9. የባንክ ብድር ወይም የግብር እዳ ባለመክፈሉ/ባለመክፈሏምክንያት ንብረቱ በሃራጅ ያልተሸጠ ተከሶ/ተከሳያልተፈረደበት/ያልተፈረደባት ወይም እሱ/እሷ የሚመራው/የምትመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት/የሆነችበትድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን/የተበደረችውንገንዘብ ባለመክፈሉ/ሏ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድርደረጃ ያልዞረበት/ባት
10. በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት/ባት
11. ታክስ ባለመክፈል ተከስሶ ጥፋተኛ ያልተባለ/ች፤
12. ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው/ያላት እንዲሁም
13. ሌሎች በመመሪያዎቹ የተገለፁ መስፈርቶችን የሚያሟሉመሆን አለባቸው፡፡

 ማሳሰቢያ

1. ጥቆማውን በባንኩ ዋና /ቤት ህንፃ 13 ፎቅ ላይበሚገኘው የኮሚቴው ጊዜያዊ ቢሮ በአካል በመቅረብወይም በመልዕክት ሳጥን ቁጥር 27002/1000.. ዘምዘም ባንክ .. የዳይሬክተሮች ቦርድአስመራጭ ኮሚቴ /ቤት  ወይም በኢሜል ZZBNEC@ZamZambank.com በመላክ ማቅረብይቻላል፡፡
2. የጥቆማ ማቅረቢያ ፎርሙ ከባንኩ ዋና /ቤትየኮሚቴው ቢሮ ወይም በባንኩ ዋና /ቤት 12 ፎቅከሚገኘው የባለአክሲዮኖች አገልግሎት ዋና ክፍል ወይምከባንኩ ድህረ ገጽ ላይ ወይም ከባንኩ ቅርንጫፎችማግኘት ይቻላል፡፡
3. ለጥያቄና ማብራሪያ በአካል መቅረብ ወይም በስልክቁጥር 0115582308 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
4. ህዳር 11 ቀን 2015 . በኋላ የሚቀርቡጥቆማዎችም ሆኑ ከዚህ ጊዜ በኋላ የሚደርሱ የጥቆማማቅረቢያ ሰነዶች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ከወዲሁበአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

 

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቅጹን ማውረድ ይችላሉ፡፡

 

Download Form