በድር ፋውንዴሽን ከሀምሌ 8 -18/2014 ዓ/ል 21ደኛ አመታዊ ጉባኤውን በኢትዮጲያ በማካሄድ ፤ለኢትዮጲያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያውን በተለይም በተለያዩ ክፍለ አለማት ለሚገኙ ሙስሊሞች የኢትዮጲያውያን ባህል እምነትና ታሪክ በመዘከር ለዓለም እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

ለአስር ቀናት የሚቆየው የበድር ኮንቬንሽን በተለያዩ ሆቴሎችና በተመረጡ ክልል ከተሞች ስብሰባና ምክክር፣ የኢትዮጲያን ታላላቅ ፕሮጀክቶች ጉብኝት በማድረግ እንደሚዘልቅ ተገልጿል፡፡ ዛሬ ቀን 8/11/2014 ዓ/ል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲከፈት ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በድር ፋውንዴሽን የኢትዮጲያ ብሄራዊ ጥቅምን ከማስከበር አንጻር ያከናወኗቸውን ተግባራት በመዘርዘር ምስጋና አቅርበውላቸውል፡፡ በመጨረሻም ፋውንዴሽኑ በሌሎችም የዴያስፖራ አባላት መደገፍ እንዳለበት እና አባላቱ የሀገር አንድነትን ሊያጠናክር በሚችል መልኩ በመከባበርና በመቻቻል ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በድር ፋውንዴሽን በሰሜን አሜሪካ ዘሬ 22 ዓመት ተቋቁሞ ከፍተኛ የሀብት ማሰባሰብ ስራ በመስራት በኢትዮጲያ ዲፕሎማሲና አድቮኬሲ ዙሪያ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ አለም አቀፍ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ፋውንዴሽን መሆኑ ይታወቃል፡፡