የሐራጅ ማስታወቂያ
ዘምዘም ባንክ አ/ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንዲሁም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተመለከቱትን በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የተበዳሪ ስም | የመያዣ ሰጪ ስም | የካርታ ቁጥር | ቤቱ የሚገኝበት ቦታ | የቦታው ስፋት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀንና ሰዓት | ጨረታው የወጣው | |
| 1. | አቶ መሀመድ አህመድ | ወ/ሮ ፈርሂያ አህመድ | 29412/14 | ጅግጅጋ ከተማ | 188.50 ካ.ሜ | 1,617,487. 4636 | 24/6/2017 ዓ.ም | ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 | ለሁለተኛ ጊዜ |
| 2. | አቶ ዛይድ ሳላህ | አቶ ዛይድ ሳላህ | 930/94/97 | ሰንዳፋ በኬ ከተማ | 3,500 ካ.ሜ | 12,221,483. 93 | 24/6/2017 ዓ.ም | ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት | ለመጀመሪያ ጊዜ |
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በዘምዘም ባንክ (አ/ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ፅሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፤ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች እና ውዝፍ የሊዝ ዕዳዎችን ይከፍላል፡፡
- ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደበዳቤ ይጽፋል፡፡
- ሐራጁ የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆሰ ክ/ከተማ ወሎ ሰፈር በሚገኘው ጋራድ ሕንፃ 13ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 06 ነው።
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም የእነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች የጨረታውን ሒደት ለመከታተል ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ቀን እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ወይም ተጫራቾች ቤቶቹን ለመጎብኘት ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥር +251 11 5582308 በመደወል መጠየቅ ይቻላል። ዘምዘም ባንክ አ/ማ



