GIFA championship award Islamic banking 2023
Global Islamic Finance Award (GIFA) is one of the most prestigious awards in Islamic banking and finance that celebrate the achievements of individuals, institutions and governments in promoting and advocating Islamic banking and finance. This year the evaluation committee for GIFA had selected ZamZam Bank for it’s contribution to establish and strengthen interest free banking in Ethiopia.
The 13th Global Islamic Finance Award (GIFA) is celebrated at an event held in Dakar, Senegal on September 14/2023 with the presence of His Excellency Macky Sall, President of the Republic of Senegal, senior ministries of various nations, ambassadors, global industry players and invited guests. It is to be remembered that last year the prime minister of Ethiopia Dr. Abiy Ahmed was the recipient of GIFA for his leadership and advocacy roles in promoting Islamic banking and finance in Ethiopia.
ZamZam bank is deeply grateful for this recognition. The bank will continue to create competitive and innovative shariah compliant products to strengthen and build the economy in our country and across the region.
Congratulations to all ZamZam bank’s board of directors, Shariah advisory council, management, staff, shareholders, customers and all ZamZam family. This award wouldn’t be possible without your dedication and trust.
ዘምዘም ባንክ የ2023 ግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንሲንግ ሻምፒዮን ሺፕ አዋርድ የክብር ሽልማት አሸናፊ ሆነ!!!! ግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንስ አዋርድ ለኢስላሚክ ፋይናንስ ዕድገት አና ለዘርፉ መስፋፋት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦች,ተቋማት እና መንግስታት በየዓመቱ የሚበረከት እጅግ ክብር ያለው ሽልማት ነዉ:: በዚህ ዓመት የግሎባል ኢስላሚክ ባንኪንግ እና ፋይናንስ ምዘና ኮሚቴ በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ ባንክ መሰረት እንዲጥል እና እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረከተው ዘምዘም ባንክ ተመርጧል:: 13ኛው ግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንስ የሽልማት ስነ ስርዓት በሴኔጋል, ዳካር ሴፕቴምበር 14/2023 የተከናወነ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ሀገራት ሚንስትሮች, አምባሳደሮች, በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ኢስላሚክ ባንክ መስፋፋት እና ማደግ ላበረከቱት የማይተካ የአመራርነት ሚና ያለፈውን ዓመት ሽልማት መውሰዳቸው የሚታወስ ነው:: ዘምዘም ባንክ ለዚህ ዕውቅና ልባዊ ደስታውን አየገለፀ, ባንካችን ተወዳዳሪ እና ዘመናዊ ቨሪዓ መር የሆኑ ለሀገራችንም ሆነ ለአካባቢው ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችሉ አገልግሎቶችን ስራ ላይ ማዋሉን አጠናክሮ ይቀጥላል:: መላው የዘምዘም ባንክ የቦርድ አባላት፣ የሸሪዓ አማካሪዎች ፣ ማኔጅመንት፣ ሰራተኞች፣ ባለ አክሲዮኖች፣ ደንበኞች እና የባንኩ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ!