The first full-fledged interest-free bank in Ethiopia

ዘምዘም ባንክ ለሐገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ በመሆን አገልግሎት ጀመረ

ለዘመናት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዘምዘም ባንክ ለሐገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ በመሆን አገልግሎት መጀመሩን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ባንካችን የሸሪአን መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አገልግሎቱንም የሚሰጡት በባንክ ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላቸው ስመጥር ባለሞያዎች ናቸው፡፡ የኮር ባንኪነግ ሲስተማችን አጅግ ዘመናዊ ሲሆን በሲስተም አቅራቢዎችና በሸሪአ ባለሞያዎች በኩል ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው ነው፡፡