The first full-fledged interest-free bank in Ethiopia

ለሁሉም የዘምዘም ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የተደረገ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ዘምዘም ባንከ አ.ማ. የባለአክሲዮኞች 4ኛ መደበኛ እና 3ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ያካሄዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካይነት በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ በመገኘት በጉባዔው ላይ እንድትሳተፉ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ማሳሰቢያ፡-

  • -በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ሥልጣን ባለው የመንግስት አካል በኩል ውክልና በመስጠት አልያም ከህዳር16 እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ድረስ ሁሌም በሥራ ሰዓት ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ፓስፖርት ወይም ቢጫ ካርድ በመያዝ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ጋራድ ሲቲ ሴንተር ህንፃ የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በግንባርበመቅረብ ለዚሁ አላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾም እና ተወካዩም በጉባዔው ላይ መሳተፍ እንዲሁም ድምፅ መስጠት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • -በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ SBB/91/2024 መሰረት የባንኩ የቦርድ አባላት እና ማንኛውም የባንኩ ሰራተኞች ከባለአክሲዮኖች ውክልና መቀበል የማችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
  • -የባንኩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ቢጫ ካርድ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው እናሳውቃለን፡፡
  • -በተጨማሪም የድርጅት ተወካዮች የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወይም ተመሳሳይ የሃላፊነት ደረጃ ላይ ያሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥማስረጃ ወይም ድርጅቱን ወክለው በጉባዔው መሳተፍ እንዲችሉ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ ጉባዔ ወይም ሥልጣን ባለውየመንግስት አካል በኩል የተሰጠ ውክልና ሰነድ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • -ለበለጠ መረጃ እንዲሁም የጉባዔውን አጀንዳዎች ለማወቅ ህዳር15ቀን 2017 የወጣውን የሪፖርተር እና አዲስ ዘመን ጋዜጦች መመልከት ይቻላል፡፡


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *