The first full-fledged interest-free bank in Ethiopia

የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት የመምረጫ መስፈርቶችን ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ

ለዘምዘም ባንክ አ/ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት የመምረጫ መስፈርቶችን ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ
የዘምዘም ባንክ አ/ማ የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ታህሳስ 5 ቀን 2018 ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ በሚሊኒየም የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ባንኩን ለሦስት ዓመታት የሚመሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ይመርጣል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 መሠረት መላው የባንካችን ባለአክሲዮኖች በዕለቱ ቢያንስ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩዎችን መጠቆምና መምረጥ እንድትችሉ ይህ የጥቆማና የምርጫ መስፈርቶችን የያዘ ማስታወቂያ ወጥቷል፡፡

የጥቆማና ምርጫ መስፈርቶች
1 የቦርድ አባላት ምርጫ ከሚደረግበት ሁለት ዓመት በፊት ባለአክሲዮን ሆኖ የተመዘገበ፤
2 በቦርድ አባልነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
3 እውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የዚያ ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያለው፤
4 በንግድ ሥራ አመራር፣ በባንክ እና/ወይም በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሕግ፣ በንግድ አስተዳደር፣ በኦዲቲንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት አስተዳደር እና በዘላቂነት ቢያንስ የሰባት (7) ዓመታት ልምድ ያለው፤
5 ታማኝ፣ ሃቀኛ፣ መልካም ዝና እና ሥነ ምግባር ያለው፤
6 ከአራት በላይ ድርጅቶች ውስጥ በቦርድ ዳይሬክተርነት እየሰራ የማይገኝና በቂ ጊዜ በመደብ ኃላፊነቱን መወጣት የሚችል፤
7 በሌላ የፋይናንስ ተቋም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሌላ ባንክ ሰራተኛ ያልሆነ፤
8 ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እምነት በማጉደል ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተሰጠው፤
9 ከባንኩ ጋር ምንም ዓይነት የጥቅም ግጭት የሌለው፤
10 የባንክ ወይም የሌላ ፋይናንስ ተቋም ብድር ወስዶ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተበላሻ ብድር የሌለው እና ግብር የከፈለ የተሳሳተ የፋይናንስ መረጃ ወይም መግለጫ ያላቀረበ፤
11 በዳይሬክተር ወይም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ የሆነበት ወይም ባለቤት በሆነበት ድርጅት የመክሰር ሂደት ያላስጀመረ ወይም መክሰሩ ያልተወሰነበት ወይም ንብረት ያልተወረሰበት፣ንብረቱ በመክሰር ውሳኔ እንዲተዳደር ያልተደረገበት ወይም የባንክ ወይም የሌላ ፋይናንስ ተቋም ብድር መክፈል በለመቻሉ ንብረቱ ለዕዳ ማስመለሻነት ያልተሸጠበት፤
12 ኃላፊነት በጎደለው ወይም በግዴለሽነት አስተዳደር፣ በማጭበርበር ወይም በሕገወጥ የንግድ ሥራ ምክንያት ኪሳራ በደረሰበት ሌላ ሰው በተገኘ ፋይናንስ ተቋም የአክሲን ግዢ ያልፈጸመ፤
13 በቂ ስንቅ ሳይኖረው የብሔራዊ ባንክ መመርያን በመጣስ ቼክ በመጻፉ በማንኛውም ባንክ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፤
14 የሚጠቆመውና የሚመረጠው የቦርድ አባል ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ ድርጅቱን በመወከል በቦርድ አባልነት የሚያገለግለው ሰው ማንነት መታወቅና ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ መሆን ይኖርበታል።
15 በተጨማሪም አግባብነት ባላቸው ሕግችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጡ መመሪያዎች ላይ የተገለጹ ሌሎች መመዘኛዎች የሚያሟላ፤ ሊሆን ይገባል፡፡

ማሳሰቢያ
• አንድ ባለአክሲዮን እራሱን በእጩነት መጠቆም ይችላል፤
• ቢያንስ ሁለት ሴቶች በቦርድ አባልነት መመረጥ ይኖርባቸዋል፤
• ከማኅበሩ ጸሐፊ በስተቀር ከሁለት የማይበልጡ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ሲኒየር ማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች የቦርድ አባል ሆነው መመረጥ ይችላሉ፤
• ከላይ የጠጠቀሱት መስፈርቶች ለህጋዊ ያለው ተቋምን ለሚወክለው የተፈጥሮ ሰውም ይሰራሉ፤
• የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ለቦርድ አባልነት መመረጥ አይችልም፤
• የቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የሚካሄደው በጉባኤው እለት ይሆናል፤
• የቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የሙያና የጾታ ስብጥርን ማረጋገጥ አለበት፤
• መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ ነባር የቦርድ አባላት በእጩነት ሊጠቆሙ ይችላሉ፤
• በጥቆማ ወቅት የጠቋሚዎች ስም እና የአክሲዮን መጠን መገለጽ አለበት፤
• የቦርድ አባላት እና የባንኩ ሰራተኞች ባለአክሲዮኖችን ወክለው ድምጽ መስጠት አይችሉም፤
• በእለቱ የጥቆማና አስመራጭ ጊዜያዊ ኮሚቴ አባላት ይመረጣሉ፡፡አስመራጭ ኮሚቴው አምስት አባላት የሚያካትት ሲሆን፣ የቦርድ አባላት እና የባንኩ ተቀጣሪ ሰራተኞች የኮሚቴው አባል መሆን አይችሉም፡፡እንዲሁም ከኮሚቴው አባላት መካከል ቢያንስ ሁለቱ ሴቶች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ያልሆኑ በለአክሲዮኖች መሆን ይኖርባቸዋል፤
• በ3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተሻሻለው የባንኩ መመስረቻ መሠረት ለባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የሚመረጡት አጠቃላይ ቁጥር 12 ናቸው፤
• በእጩነት የሚቀርቡት የቦርድ አባላት ቁጥር በጠቅላላው 24 ሲሆኑ፤ከእነዚሁም ውስጥ 8 እጩዎች ለገለልተኛ የቦርድ አባልነት ሲሆኑ እነዚሁንም እጩዎች የሚጠቆሙት ስራ ላይ ባለው ቦርድ ይሆናል፡፡የተቀሩት 16 እጩዎች የሚጠቆሙት ደግሞ በሁሉም ባለአክሲዮኖች ይሆናል፤
• ባንኩ በብሔራዊ ባንክ መመዘኛ መሰረት ባንኩ ተጽእኖ ፈጣሪ የሚሰኙ ባለአክሲዮኖች ለጊዜው ስለሌሉት የቦርድ ምርጫና ጥቆማ ሂደት በተለያዩ ምድቦች ከፋፍሎ ማካሄድ ስለማያስፈልግ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ የቀረቡት እጩዎች በሁሉም በባለአክሲዮኖች በአንድ ምድብ የሚጠቆሙና የሚመረጡ ይሆናሉ፤
• የድምፅ ቆጠራው ውጤት በዚያው ቀን ለጠቅላላው ስብሰባ ይገለፃል እንዲሁም በቀጣዩ የሥራ ቀን በባንኩ ዋናው መ/ቤት የማስታወቂያ ሰሌዳ እና ድረ-ገጽ ላይ ይለጠፋል፤
• በእለቱ ለቦርድ አባልነት ለመወዳደር የሚፈልጉ ባለአክሲዮች አግባብነት ያላቸውን የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃዎቻቸው ኮፒ በጉባኤው ይዘው እንዲቀርቡ ይመከራል፤
• የቦርድ አባላት ጥቆማ ምርጫ ሂደት አግባብነት ባላቸው የሃገሪቷ ህጎች፣ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ እና በባንኩ የቦርድ አባላት የጥቆማና የምርጫ ደንብና የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት የሚመራ ይሆናል፤
• ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +2515582308 በመደወል ወይም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ፣ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ወረዳ 02፣ጋራድ ሲቲ ሴንተር ሕንጻ፣ 13ኛ ወለል፣ቢሮ ቁጥር 06 ከሚገኘው የማኅበሩ ጸሐ ፊ ቢሮ በአካል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

ዘምዘም ባንክ አ/ማ
የማይነጥፍ የዕድገት ምንጭ!


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *