The first full-fledged interest-free bank in Ethiopia

ለዘምዘም ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የዘምዘም ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ  ጠቅላላ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታኅሣሥ  16 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጧቱ  3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ  7፡00 ሰዓት በሚሊኒየም  አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም፣ የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡       

 

የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የጉባኤዉን ድምጽ ቆጣሪዎችን መሠየም፤
  2. የጉባኤውን ፀሀፊ መሠየም፤
  3. ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ፤
  4. የጉባኤዉን አጀንዳ ማፅደቅ፤
  5. አ.ኤ.አ. በ2021/2022 የተካሄዱትን የአክሲዮን ዝውውሮችን መቀበል እና ማፅደቅ፤
  6. የባንኩን ዓመታዊ የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት መስማትና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
  7. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት መስማትና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ የአሰራር መመሪያ ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ፤
  10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን የአገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን፤
  11. የአስመራጭ ኮሚቴ አገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን፤
  12. የባንኩን የውጭ ኦዲተሮች መሾምና ክፍያቸዉን መወሰን፤ እና
  13. በጉባኤዉ ላይ የተያዘዉን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

 

አስቸኳይ  ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የጉባኤውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየም፤
  2. የጉባኤውን ፀሀፊ መሰየም፤
  3. ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ፤
  4. የጉባኤዉን አጀንዳ ማፅደቅ፤
  5. በባንኩ መተዳደሪያ ደንብና መመስረቻ ጽሁፍ ላይ ማሻሻያ ማድረግ፤ እና
  6. በጉባኤዉ ላይ የተያዘዉን ቃለጉባኤ ማፅደቅ፡፡

 

                                                                                      የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ሰብሳቢ

                                                                                                 ዘምዘም ባንክ አ.ማ.


Contact information

Ethiopia’s first with a full interest-free license, shaping ethical finance for a brighter future

Copyright © 2024 ZamZam Bank. All Rights Reserved.

  • About Us
  • Products & Services
  • Digital Banking
  • Media
  • Help?