The first full-fledged interest-free bank in Ethiopia

ለዘምዘም ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የዘምዘም ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 5 ቀን 2018 ከጧቱ 200ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

  1. ባንኩን የተመለከቱ መረጃዎች

1.1.የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ፣ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ወረዳ 03፣ጋራድ ሲቲ ሴንተር 11-13ኛ ፎቅ፣

1.2. የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር MT/AA/3/0052093/2012 የተመዘገበ

1.3. የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ካፒታል ብር 2,655,538,000.00

1.4. የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ካፒታል ብር 2,655,538,000.00

1.5. የድረ-ገጽ አድራሻ www.zamzambank.com

2.የ5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

2.1. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ፤

2.2. እ.ኤ.አ. በ2024/2025 የተካሄዱ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅና እና አዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤

2.3. የቦርድ አስመራጭ ጊዜያዊ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ፤

2.4. ከአክሲዮን ሽያጭ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ባንኮች በተከፈቱ ዝግ ሂሳቦች ውስጥ ተቀምጠው በሚገኙ ገንዘቦች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤

2.5. እ.ኤ.አ. የ2024/2025 የዳይሬክተሮች ቦርድን ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ መወሰን፤

2.6. እ.ኤ.አ. የ2024/2025 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ መወሰን፤

2.7. እ.ኤ.አ. የ2024/2025 የሂሳብ ዘመን በተገኘው ትርፍ አመዳደብና አከፋፈል ላይ መወያየትና ውሳኔ ማሳለፍ፤

2.8. እ.ኤ.አ. 2024/2025 የሂሳብ ዘመን የባንኩ የውጭ ኦዲተር ያከናወነውን ሥራ አስመልክቶ ባቀረበው የክፍያ ጭማሪ ጥያቄ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤

2.9. እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የባንኩን የውጭ ኦዲተር መሾምና ክፍያውን መወሰን፤

2.10. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2024/25 ዓመታዊ የሥራ ዋጋ እና የ2025/26 የሚከፈላቸውን ወርሃዊ አበል መወሰን፤እና

2.11. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ፡፡

3. 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

3.1. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ፤

3.2. በመጠባበቂያ ሂሳብ ላይ የሚገኘውን ገንዘብ ወደ ባንኩ ካፒታል እንዲዞር ተወያይቶ መወሰን፤እና

3.3. የባንኩን ካፒታል ማሳደግ፤

3.4. ስለውህደት እና ግዢ አፈጻጻም ላይ ውይይት ማድረግና ተገቢውን መወሰን፤ እና

3.5. በባንኩ መመሥረቻ ጽሑፍ ላይ ማሻሻያ ማድረግ፡፡

ማሳሳቢያ

  • የባንኩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ፋይዳ መታወቂያ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • በጉባኤው ላይ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ በተሰጠ የውክልና ሰነድ(ተወካይ ዋናውና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የተወካዩን ማንነት የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ወይም ፋይዳ ካርድ በመያዝ) ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከመካሄዱ ሦስት ቀን በፊት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በጋራድ ሲቲ ሴንተር ህንፃ ምድር ቤት የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል እና በባንኩ ቅርንጫፎች በግንባር በመቅረብ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት መወከል ይችላል፡፡
  • እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው የባንኩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀን ያላለፈበት መታወቂያ ወይም ቢጫ ካርድ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክበሮት እንገልጻለን፡፡
  • አንድ ባለአክሲዮን በባንኩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ተወካይ ብቻ ነው፡፡ሆኖም ስራ ላይ ያለው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም የባንኩ ሰራተኛ የባለአክሲዮኖች ተወካይ ሆኖ ሊወከል የማይችል መሆኑን እናሳውቃን፡፡
  • በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅ በተደነገገው መሠረት ተገቢውን የባለአክሲዮኖች መረጃ ለማሟላት እንዲረዳ ባለአክሲዮኑ ወይም ተወካይ የባለአክሲዮኑን የዲጂታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ኮፒ ይዘው እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
  • ለምዝገባ ቅልጥፍና ሲባል ባንኩ የባለአክሲዮኖቹን መለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚልክ ሲሆን፤የመለያ ቁጥራቹን በስብሰባው እለት ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአጽዕኖት እንጠይቃለን፡፡

የዘምዘም ባንክ አ/ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

ዘምዘም ባንክ

የማይነጥፍ የእድገት ምንጭ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *