ዘምዘም ባንክ ከአዲስ ቻምበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ!

ዘምዘም ባንክ ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። የዚህ ስምምነት ዋና ዓላማ የባንኩን ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎቶች ለንግዱ ማህበረሰብ በተለይም ለአነስተኛና መካከለኛ ነጋዴዎች ተደራሽ ማድረግ ነው።
ይህንን ስምምነት ያደረጉት የዘምዘም ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ እና ወ/ሮ ዘሐራ መሀመድ የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ናቸው።
በዚህ ስምምነት መሠረት ባንኩ ከክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ጋር በጋራ ባበለጸገዉ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በሚተገዘዉ አንሳር በተሰኘው የፋይናንስ ስርዓትን በመጠቀም ከማስያዣ ነፃ የሆኑ የፋይናንስ አማራጮችን ለንግዱ ማህበረሰብ ያቀርባል።
ከዚህ በተጨማሪም ፤ የንግዱ ማህበረሰብ ከባንኩ ያለ ማስያዣ ከ60 ሺህ ብር እስከ 1 ሚሊየን ብር የሚደርስ ብድር ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
በስምምነቱ ወቅት እንደተገለፀዉ ፤ ባንኩ እና ም/ቤቱ የንግዱን ማህበረሰብ ችግሮች በመለየት ተገቢውን የፋይናንስ መፍትሄ ለመስጠት በጋራ እንደሚሰሩ ታውቋል።
አምስት ዓመታት በፅናት፣ ወደ ላቀ ምዕራፍ!
ዘምዘም ባንክ
የማይነጥፍ የእድገት ምንጭ!













