የነገዋን ለምለም ኢትዮጵያ ለመገንባት ዛሬ ተስፋን እንተክላለን!

ዘምዘም ባንክ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በርካታ ችግኞችን በመትከል አሻራውን አሳርፏል።
በዚህ ሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ የ800 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር የመትከል ታሪካዊ መርሃ-ግብር ላይ የባንኩ የማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ስነ ስርዓት አከናውኗል።
ይህ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪና ታሪክ አካል በመሆን ለአካባቢያችን ጥበቃና ለሀገራችን አረንጓዴ ልማት የድርሻችንን ከመወጣት ባለፈ ለመጪው ትውልድ ምቹ እና የበለጸገች ሀገርን ለማስረከብ ከሚደረገው ርብርብ አኳያ መሰል መርሀ ግብሮች ፋይዳቸው ላቅ ያለ መሆኑን ባንካችን በፅኑ ያምናል።
በመጨረሻም ለዚህ መርሀ ግብር መሳካት ተሳትፎ ላደረጉ ባለ ድርሻ አካላት እንዲሁም ለባንካችን አመራር እና ሰራተኞች በዚህ አጋጣሚ ምስጋናችንን ለማድረስ እንወዳለን።
በማይነጥፍ ፅናት፣ ወደ ላቀ ምዕራፍ!
ዘምዘም ባንክ — የማይነጥፍ የእድገት ምንጭ!














