The first full-fledged interest-free bank in Ethiopia

ዘምዘም ባንክ 5ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በይፋ አስጀመረ! “5 ዓመታትን በፅናት፤ ወደ ላቀ ምዕራፍ!”

ከጅምሩ እስከ ዛሬ ድረስ የተጓዝንበትን መንገድ የምናስታውስበት፣ ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች የምናከብርበት ልዩ ወቅት ላይ ነን!

የባንኩ የቦርድ አባላት፣ የሸሪዓ አማካሪዎች፣ አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድነት በተገኙበት በዚህ የክብረ በዓሉ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ ባንካችንን ልዩ የሚያደርጉት ቤተሰባዊ የስራ ከባቢ እና ጠንካራ ታሪካዊ ጉዞ በስፋት ተነስተዋል።

የዘምዘም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ናስር ዲኖ “ይህን ታሪካዊ ባንክ እውን እንዲሆን ብዙ ተግዳሮቶችን አልፈናል፤ የዜጎችን ህይወት የሚለውጥ፤ ባንኩን ለትውልዶች የሚተላለፍ ተቋም በማድረግ ለአላማ መቆም ምንጊዜም አስፈላጊ ነው።” ካሉ በኋላ፣ እስከዚህ የተደረሰው ስኬት የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ውጤት መሆኑን በመግለጽ ለባንኩ ቤተሰቦች በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የዘምዘም ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ ለዚህ ስኬት አሻራቸውን ላኖሩ የባንኩ አመራሮች እና ሰራተኞች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ባንኩ የመጀመሪያውን የአምስት ዓመት ጉዞ በስኬት አጠናቅቆ የቀጣዩን ሁለተኛ ዘመን ስትራቴጂ እቅድ ከዛሬ ጀምሮ ይፋ ማድረጉን ገልጸው፤ ይህንን ወደ ላቀና ጠንካራ ስራ የሚያሸጋግረንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለብን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም፣ ወ/ሮ መሊካ ለዘምዘም ባንክ ስኬት ዓይነተኛ ድርሻ ላበረከቱት መላው ባለድርሻ አካላት፣ ባንኩ የዘንድሮን በጀት ዓመት በሁሉም መለኪያዎች ከ100% በላይ በሆነ ስኬት በማጠናቀቁ “እንኳን ደስ አላችሁ!” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ይህ መርሀ ግብር በተለያዩ ዝግጅቶች ለሚቀጥሉት ወራት ደምቆ የሚቀጥል ይሆናል::


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *