ZamZam Bank Officials at 12th GIFA Awards 2022
Our bank’s Board Chairman, Dr. Nassir Dino and President, Ms. Melika Bedri were invited by the organizers of GIFA to participate and accompany Dr. Yahia Abdul Rahman, our bank’s global Sharia’h advisor, at the 12th Global Islamic Finance Award.
Dr. Yahia has received prestigious award for his outstanding achievements and contributions to the development of Islamic banking and finance as a sustainable system within the global Islamic financial architecture. However he presented this award to our bank as a sign of courtesy and gratitude.
On behalf of ZamZam’s board, management and staff, we would like to congratulate Dr. Yahia for his great achievement and express our appreciation for honoring our bank.
የዘምዘም ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር ናስር ዲኖ እና የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ፣ በ12ኛው የዓለም ኢስላሚክ ፋይናንስ ሽልማት ላይ እንዲሳተፉ እና ከባንካችን የዓለም አቀፍ የሸሪዓ አማካሪ ዶ/ር ያህያ አብዱል ራህማን ጋር በአብሮነት እንዲገኙ በፕሮግራሙ አዘጋጆች ተጋብዘዋል።
ዶ/ር ያህያ በዓለም አቀፍ ኢስላሚክ የፋይናንስ መሠረት ላይ ዘላቂነት ያለው አሠራር በማምጣት ለኢስላሚክ ባንክ እና የፋይናንስ ልማት ላበረከቱት ከፍተኛ ስኬት እና አስተዋፅዖ የክብር ሽልማት አግኝተዋል። ዶ/ር ያህያ ሽልማታቸውን በአክብሮት፣ በመነሳሳት እና በታታሪነት ተምሳሌት ለባንካችን አበርክተዋል፡፡
ዶ/ር ያህያ ለዚህ ታላቅ ስኬት በመብቃታቸው በዘምዘም ባንክ የቦርድ አባላት፣ አመራሮችና ሠራተኞች ስም የተሰማንን ደስታ እየገለጽን፤ ይህንን የተምሳሌት ሽልማት ለባንኩ ስላበረከቱልን ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።