አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወለድ አልባ ባንክ የስራ ፍቃድ ርክክብ በዘምዘም ባንክ እና ብሄራዊ ባንክ መካከል ተደረገ። ዘምዘም ባንክ ከ13 አመታት የአክሲዮን ምስረታ በኋላ ወደስራ የሚያስገባውን ፍቃድ ዛሬ አግኝቷል። ባንኩ በዘርፉ ከፍተኛ የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጁነት አላቸው ያላቸውን ወይዘሮ መሊካ በድሪን ዋና ስራ አስፈጻሚው አድርጎ አስተዋውቋል።
በዛሬዉ እለት የባንክ ንግድ ሥራ ፈቃድ በብሔራዊ ባንክ ገዠ ክቡር ዶ/ር ይናገር ደሴ እጅ በስካይ ላይት ሀቴል በተደረገ ደማቅ ሥነ ሥርዓት ለዘምዘም ባንክ ተሰጥቷል። የባንኩ ገዥ ባደረጉት ንግግር በሀገራችን የመጀመሪያዉ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ ለሆነዉ ዘምዘም ባንክ በልዩ ዝግጅት ፈቃዱን ለመስጠት ያስፈለገዉ ከበርካታ አመታት ድካምና ትእግስት በሗላ እዉን የሆነዉ ይህ ባንክ በሀገራችን የተጀመረዉ ለዉጥ ማሳያና በመስኮት ሲሰጥ ለቆየዉ የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የበለጠ ድምቀትና ጥንካሬ የሚፈጥር መሆኑን ለማመልከት ጭምር ነዉ ብለዋል። የወለድ ነፃ ባንክ በእምነታቸዉ ምክንያት ከወለድ ጋር ለመተሳሰር ለማይፈልጉ ዜጎቻችን ብቻ ሳይሆን አገልግሎቱን ለሚሹ ሁሉ ታላቅ ስጦታ ነዉ ብለዋል- ክቡር ዶ/ር ይናገር ደሴ።
Ac tortor vitae purus faucibus ornare supendisse sed nisi. Pretium aenean phareta gna ac placerat vestibulum lectus mauris. Rhoncus aenean vel elit scelerisque mauris pentesque pulvinar. Euismod elementum nisi quis eleifend quam. Turpis tincidunt id aliquet risus feutgiat in ante. Ac tortor vitae purus faucibus ornare suspendisse sed nisi.
My wishlist for the new Zamzam Bank HQ online fill-out forms PLEASE SELECT YOUR […]
Memorandum of Association And Article of Association